በጽንፈኛው ጁንታ የሕወሓት ኃይል ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ኦፕሬሽን በስኬት እንደተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታውቀዋል።
የአየር ኃይሉ በወሰደው እርምጃም በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ለማውደም መቻሉንም ገልፀዋል።
እነዚህ ሮኬቶች እስከ 300 ኪሎ ሜትሮች መወንጨፍ የሚችሉ በመሆናቸው እና በወንጀለኛው ቡድን ሮኬቶቹን የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ በመቐለ እና አካባቢዋ በነበረው የከባድ መሣሪያ ማስቀመጫ ላይ የአየር ኃይሉ እርምጃ እንዲወስድ መደረጉ ተገልጿል።
(ምንጭ፡-ኢብኮ)