የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ለተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶች በሰጠው ማብራሪያ ችግሩ በቶሎ እንዲቀረፍ ያላቸውን ምኞት መግለጻቸው ተጠቁሟል፡፡

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፉት ሳምንታት ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ ባለፉት ሳምንታት ድርድር ሲያካሂዱ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልጸዋል፡፡

በድርድሩ ላይ አፍሪካዊያን ኤክስፐርቶች እንዲሳተፉ የቀረበውን ሃሳብ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ሲስማሙ ግብጽ ግን አለመስማማቷን አምባሳደር ዲና ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ከተለያዩ ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ተግባራትን ማከናወኗንም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

የጂቡቲ የኢነርጂ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ሃገራቸው ከኢትዮጵያ የምትገዛው የኤሌክትክ ሃይል አቅርቦት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያላትን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

በሌላም በኩል የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብልፈታህ አልቡርሃን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉትም ባለፉት ሳምንታት ውስጥ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት ፍጹም ሰላማዊ መሆኑንም አምባሳደር ዲና አስረድተዋል፡፡

(በመስከረም ቸርነት)

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board.

Leave a Reply