👉የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ሆይ የስግብግቡን ጁንታ ግብአተ መሬት ለመፈፀም በመጨረስ ላይ እንገኛለን፤ 

👉ጁንታው ቡድን በሁሉም አቅጣጫ ተከቧል፤ መውጫና መግቢያ አጥቶ ታፍኖ የሞት ጣር ላይ  ይገኛል፤ 

👉ባሁኑ ሰአት ስግብግቡ ጁንታው አመራር ለመስጠት በማይችልበት ደረጃ ደርሶ ይገኛል፤ ልጆችህ ያለ ምግብ እና ውሃ የሞት እራት እየሆኑ ነው ስለዚህ ልጆችህ ሂወታቸውን እንዳይሰጡ በፍጥነት አድን፤ 

👉የልጆችህ ሞት የጁንታውን እድሜ ለሰአታት ወይም ለቀናት ከማራዘም ውጪ ምንም ትርጉም የለውም፤ 

👉ሰው ለሃገር እና አለማ እንጂ ለጥፋት ቡድን ብሎ ሊሞትና አካሉ ሊጎድል አይገባም፤ 

👉ከትግራይ ህዝብ በላይ የጦርነት አስከፊነት የሚያውቅ የለም፤ ጁንታው ቡድን ለራሱ አይሞትም አካሉም አይጎድልም ስለዚህ የልጆችህ ደም ለጁንታው ቁማር መጫወቻ መሆን የለበትም፤ 

  👉 የልጆችህን ውድ ህይወወት ለማትረፍና ከአንበጣ የቀረውን እህልህን ወደ መሰብሰብ  እንድትመለስ ተጋግዘን ጁንታውን ቡድን ቶሎ ልንጨርሰው ይገባል ብዬ ጥሪዬን አቀርባለሁ፤ 

👉የተከበርከው የትግራይ ህዝብ ስግብግቡን ጁንታ ቶሎ መተን ወደ ልማታችን ልንመለስ ይገባል ስለዚህ የወጣት ልጆችህን ህይወት ቶሎ አድን፤ እያደረከው እንዳለሀውም መከላከያ ሰራዊትን አግዝ፤ 

👉በመስዋእትነት የገነባሀትን ኢትዮጵያ አሁንም በማዳን ታሪክህን  እንድታድስ ውድ አገርህ ጥሪ አድርጋልሃለች፤ 

👉በተለያየ የአመራር እርከን ያላችሁ ሲቪል መሪዎች ያለን ተቃርኖ በህወሓት ተሰግስገው ካሉ ጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ ስለሆነ ራሳችሁን ከዚህ ጁንታ እንድታርቁ ጥሪ ቀርቦላችኋል፤ 

👉 መላው የትግራይ የፀጥታ አባላት በሙሉ ባለፉት ጥቂት ቀናት የገጠማችሁን አይታችኋል የስርአቱ ተጠቃሚዎች ወደ ሞት እያሰገቧችሁ ነው፤ እነሱ እየበሉ እየጠጡ እየተኙ እናንተ ግን በባዶ ሆዳችሁ የጥይት እራት እየሆናችሁ ነው፤ 

👉ጁንታው ቡድን አይደለም ደማቸውን ለመስጠት ሂወታቸውን ለመገበር ይቅርና የተኩስ ድምፅ ለመስማት እንኳ አይፈልጉም፤ ታድያ ለየትኛው አለማ ነው ወጣትነታችሁ በከንቱ የምታጠፉት፣ ለምን ትግራይን የወላድ ድሃ ታደርጓታላችሁ፣ ለምንስ ጉልበታችሁን ልማት ላይ አታውሉትም፣ 

👉ለዚህ ቀናት የቀሩት ጁንታ ቡድን ብላችሁ ህይወታችሁን ልትገብሩም ሆነ ደማችሁን ልታፈሱ በፍፁም ኣይገባም፤ 

👉 እጃቹህ ለመከላከያ በመስጠት አገራችሁ የሰጠቻችሁን እድል ሳያመልጣችሁ በሁለት ሶስት ቀናት ራሳችሁን አድኑ፤ 

ኢትዮጵያ በእውነተኛ ልጆችዋ ታሸንፋለች!

By Eyasu Esayas

Entrepreneur, Writer, Business advocate and Teacher. Nice to have every soul on board.

Leave a Reply